Pip Reid / Bible Pathway Adventures
ጂዊሽ ቮይስ ኢንተርናሽናል ከባይብል ፓዝ ዌይ አድቬንቸርስ ጋር በመተባበር በዓለም ዙሪያ ላሉ ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛዎችን ለማዘጋጀት ይሠራል፡፡ ዜሕራ ሕፃናት በተሰኘው የትምህርት ፕሮግራማቸው በኩል፣ ይህ መሥሪያ መጽሐፍ በሰማያዊ ጥሪ እና ዓላማ ያድጉ ዘንድ ትውልድ እንዲባረክበት እንጸልያለን።ባይብል ፓዝዌይ አድቬንቸርስ አዝናኝ በሆነና ፈጠራ በታከለበት መንገድ ለልጆች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት እንዲያስተምሩ መምህራንን ይረዳል፡፡ ይህንንም የምናደርገው www.biblepathwayadventures.com በተሰኘው ዌብሳይታችን ውስጥ በሚገኙ ስዕላዊ የታሪክ መጻሕፍት፣ መሥሪያ መጻሕፍትና በሌሎች ሕትመት ውጤቶች አማካኝነት ነው።